You are currently viewing Annual Meeting of the National Committee for the Man and Biosphere Reserve was Held

የሰውና ባዮስፌር ሪዘርቭ ብሔራዊ ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባ ተካሄደ

የሰውና ባዮስፌር ሪዘርቭ ብሔራዊ ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባ መጋቢት 03 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተካሄደ፡፡

ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን Mr. Mashaleni, ከ UNESCO-Addis Ababa Laission office መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የያዮ ባዮስፌር ሪዘርቭ ወቅታዊ የክለሳ ሰነድ ቀርቦ በሙሉ ድምጽ የጸደቀ ሲሆን የአኙዋ ባዮስፌር ሪዘርቭ እንዲቋቋም የእጩነት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የከፋ እና ሸካ ባዮስፌር ሪዘርቮችን የተመለከተ ሰነድ ከቀረበ በኋላ የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦች ቀርበው ስብሰባው ተጠናቋል፡፡