You are currently viewing The implementation of the biodiversity centers plan was reviewed

የብዝሀ ሕይወት ማዕከላት እቅድ አፈፃፀም ተገመገመ

በወካይ የግብርና ሥርዓተ ምህዳሮች የተቋቋሙት የብዝሀ ሕይወት ማዕከላትና የእጽዋት አጸዶቻችን የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን፤ መልካም ዉጤቶችን በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም ለብዝሀ ሕይወት ጥበቃና ዘለቄታዊ አጠቃቀም ቁልፍ ሚና እንዲጫወቱ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት 7 ማዕከላት፣ ሁለት የእጽዋት አጸዶችና አንድ ዱፕልኬት ዘረመል ባንክ ያሉት ሲሆን፤ በቀጣይ ዓመታት በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ሁለት ተጨማሪ ማዕከላትን ለመክፈት በዝግጅት ላይ ነዉ።