You are currently viewing The implementation of the 2015 plan and the 2016 budget plan were discussed

የ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 ዓ.ም የበጀት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተደረገ

የ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 ዓ.ም የበጀት ዕቅድ ዙሪያ ከማኔጅመንት አባላት እና ከማዕከላት አስተባባሪዎች ጋር ነሀሴ 09-10 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰበያ አዳራሽ ውይይት ተደረገ፡፡

ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የ2015 ዓ.ም ስኬቶችንና ተግዳሮቶችን እንዲሁም በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገባቸውን ተግባራት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

አቶ ማስረሻ የማነ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ የ2015 ዓ.ም የኢንስቲትዩቱን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2016 ዓ.ም የበጀት ድልድል ዕቅድን ለውይይት አቅርበዋል፡፡

ወ/ሮ አልማዝ ከበደ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ በበኩላቸው በ2015 ዓ.ም ከግዥና ፋይናንስ፣ ከሰው ኃብት አንጻር፣ ከመሰረታዊ አገልግሎት እና ከአመራር አንጻር በየማዕከላት የታዩ ክፍተቶችን ያቀረቡ ሲሆን አቶ ግሩም ፋሪስ የማዕከላት እና እጽዋት አጸድ አስተባባሪ የ2015 የማዕከላት ሱፐርቪዥን ሪፖርትን ለውይይት አቅርበዋል፡፡

ለቀረቡ ጥያቄዎች የሚመለከታቸው አካላት ምላሾችን የሰጡ ሲሆን ማዕከላት ከዋና ስራ አስፈጻሚዎች ጋር የ2016 ዓ.ም ተግባራት ዕቅድን የጋራ በማድረግ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡