You are currently viewing The Post-2020 International Biodiversity Framework Promotion Consultation Forum was held

የድህረ-2020 ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ማዕቀፍ ማስተዋወቂያ የምክክር መድረክ ተካሄደ

የድህረ-2020 ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ማዕቀፍ ማስተዋወቂያ የምክክር መድረክ ተካሄደ

የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ዶ/ር ምስክር ተሰማ የGBF-EAS ፕሮጀክት አስተባባሪ ያቀረቡ ሲሆን ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

የድህረ-2020 ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ማዕቀፍ ሂደትና የተገኙ ውጤቶችን የተመለከተ ሰነድ ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሲያቀርቡ GBF-EAS ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የተሰኘ ሰነድ ዶ/ር ምስክር ተሰማ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የብሔራዊ ስርዓተ-ምህዳር ዳሰሳ ሂደቶች፣ አተገባበርና የተገኙ ውጤቶችን ያካተተ ሰነድ ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ያቀረቡ ሲሆን የብሔራዊ ስርዓተ-ምህዳር መጽሀፍ የምረቃ ስነ-ስርዓት ተከናውኗል፡፡

በመጽሀፉ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና ስነ-ስርዓት ተከናውኖ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡