የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነውን የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ በሸገር ከተማ አስተዳደር በገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ነሀሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም አከናወነ፡፡
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን አስመልክቶ ዶ/ር ካርታ ካስኬ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት ሰው ተኮር ተግባራትን በማከናወን ማህበራዊ ኃላፊነታችንን እንወጣለን ካሉ በኋላ በቀጣይም በትብብር መሰል ተግባራት እንደሚከናወኑ ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ ቦጌ ኬኔ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ በበኩላቸው የመኖሪያ ቤት ዕድሳት ድጋፍ ለማድረግ በመምጣታችሁ በራሴና በክፍለ ከተማው ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ መሰረት ዶ/ር ካርታ ካስኬ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና ወ/ሮ ቦጌ ኬኔ የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታውን ያስጀመሩ ሲሆን የዲዛይን ርክክብም ተከናውኗል፡፡
አቶ ማስረሻ የማነ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ በቀጣይ ለተማሪዎች ድጋፍ ስለሚደረግ ት/ቤቱን የመጎብኘት አስፈላጊነት አስታውሰዋል፡፡
መ/ር ታደሰ አሰፋ የጌጃ ቤኛ 1-8ኛ ት/ቤት መምህር በጉብኝቱ ወቅት ያሉበትን ተግዳሮቶች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
ከት/ቤቱ ጉብኝት በኋላ ዶ/ር ካርታ ካስኬ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቅም በፈቀደ መልኩ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡
