የአርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት አዋጅ መነሻ ክፍል 1 | ክፍል 2 | ክፍል 3 | ክፍል 4 | ክፍል 5 | ክፍል 6 | ክፍል 7

ለንግድ ዓላማ የጀነቲክ ሀብት አርክቦት ማመልከቻ

የጀነቲክ ሀብትና የማህበረሰብ ዕዉቀት አርክቦት መብቶች አዋጅ ቁ.482/1998 እና ደንብ ቁ. 169/2ዐዐ1 መሠርት ጀነቲክ ሀብትን ለንግድ ዓላማ ለመጠቀም የሚፈልግ አመልካች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አሟልቶ ሊያቀርብ ይገባል፡፡

  1. ጠቅላላ መረጃ
    • የአርክቦት አመልካች (Natural/Legal Person) ስም፣ የተመዘገበ አድራሻ፣ የትምህርት መረጃ/ሙያ (Curriculum Vitae)፣ የድርጅት ማቋቋሚያ ሰነድ፤
    • ለማመልከቻው ትክክለኛነት ተጠያቂ የሚሆነው ሰው፣ ኃላፊነት፣ ሙሉ አድራሻ አና ፊርማ፤
  2. ዝርዝር መረጃ /ገንዘብ ነክ እና የቴክኒክ መርጃ/
    • የአርክቦት ኘሮጀክቱ በጀት፣ የአርክኮት ኘሮጀክቱን የደገፉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ዝርዝር፤
    • የጀነቲክ ሀብቱ ሳይንሰዊ መረጃ (Scientific name)፤
    • የጀነቲክ ሀብቱ/ ውጤት (Genetic Resource/derivatives)፣ የሚሰጠው/ወደፊት ሊሰጥ የሚችለው ጠቀሜታ፤
    • የጀነቲክ ሀብቱ ሊሰበሰብ የታሰበበት አካባቢ እና ሌሎች ሊገኝ የሚችልባቸው አካባቢዎች ዝርዝር (የሚታወቅ ከሆነ)፤
    • ለማርከብ የተፈለገው ጀነቲክ ሀብት መግለጫ /ሕብረ ህዋስ፣ ዘር፣ ቅጠል፣ ወዘተ
    • የሚሰበሰበው ጀነቲክ ሀብት መጠን /በኪሎ ግራም፣ ሊትር፣ ወዘተ/፤
    • ከጀነቲክ ሀብቱ ጋር ተያይዞ የሚገኘው የማህበረሰብ ዕውቀት (ካለ)፤
    • አርክቦት የሚፈጸምበት የጀነቲክ ሀብት የሚገኘው በኢዘቦታ ከሆነ፣ የጀነቲክ ሀብቱን ይዞ የሚገኘው ተቋም ማንነት፤
    • የጀነቲክ ሀበቱ ሊውል የታሰበበት ጠቀሜታ/ዓላማ፤
    • የምርምሩ ዓይነትና ጥልቀት፣ ጥቅም ላይ የሚዉለዉ የባለሙያና የመሣሪያ ዓይነት፤
    • ከምርምሩ የሚጠበቀው ዉጤትና ምርምሩ የሚወስደው ጊዜ /በግምት/፤
    • የምርምሩና የማልማት ሥራው የሚካሄዱባቸው ቦታዎች፤
    • ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በምርምሩ ውስጥ የሚሳተፉ ከሆነ የሚሳተፉበት ሁኔታ እና የተሳትፏቸዉ መጠን፣
    • በምርምሩ ውስጥ ሊሳተፉ እና ሂደቱን ሊቆጣጠሩ የሚችሉ ኢትዮጵያዊያን ተቋማት እነማን እንደሆኑ /ሊታወቅ የሚችል ከሆነ/፤
    • የጀነቲክ ሀብቱ/ውጤቱ መጀመሪያ እና በቀጣይነት ሊወሰድ የሚችልባቸው ቦታዎች፤
    • የአርክቦት አመልካቹ የዉጭ ሀገር ዜጋ ከሆነ፣ ከሀገሩ መንግሥት ሥልጣን ያለዉ አካል አመልካቹ የአርክቦት ፈቃድ ቢሰጠው የአርክቦት ግዴታዎች በዚያ ሀገር የሚያስከብርና የሚያስፈጽም መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤
    • ለሀገሪቱ ወይም ለሚመለከተው የአካባቢ ማህበረሰብ ያስገኛል ተብሎ የታሰበው ወይም ሊያስገኝ የሚችለው ኢኮኖሚያዊ፣ ቲክኖጂ፣ ሳይንሳዊ፣ አካበቢያዊ ወይም ሌሎች ማናቸውም ጥቅሞች ሊያካትት ይገባል፡፡

    ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አድራሻዎች ማግኘት ይችላሉ፡፡
    ኢ-ሜይል፡ info@ebi.gov.et
    Tel: +251-11-6612244
    ፋክስ፡ +251-11-6613722
    አዲስ አበባ