የብዝሀ ሕይወት ማዕከል ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ!

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አመሰራረት

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት እ.ኤ.አ ግንቦት 1976 በኢትዮጵያና በጀርመን መንግስት መካከል በተደረገው የትብብር ስምምነት መሠረት የእጽዋት ጀነቲክ ሀብት ማዕከል (A Plant Genetics Resource Center) በሚል ለመጀመሪያ ጊዜ ተቋቋመ፡፡ ዋና ዓላማውም የሀገሪቱን የዕጽዋት ሀብቶች ከሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች መጠበቅና የሰብል ምርቶችን ለማሻሻል ነበር፡፡ ቀጥሎም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. አፕሪል 5/1994 54ኛዋ ሀገር ሆና የዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት ስትፈርም ይህንን ለማስፈፀም ይቻል ዘንድ በእጽዋት ላይ ብቻ ሲሰራ የቆየውን የእጽዋት ጀነቲክ ሀብት ማዕከል (PGRC/E) የእንስሳትና የደቂቅ አካላት እንዲጨምር ተደርጎ ሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምር ኢንስቲትዩት (EBIR) በሚል በአዲስ መልክ ተመሰረተ፡፡ እ.ኤ.አ በ2004 በአዲስ መልክ ጥበቃ ላይ እንዲያተኩር ታስቦ የብዝሀ ሕይወት ጥበቃ ኢንስቲትዩት (EBI) በሚል ተቋቋመ፡፡ በመጨረሻም አሁን የያዘውን ቅርጽ በመያዝ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በሚል እኤአ በ2013 ተቋቋመ፡፡

ኃላፊትነት፣ ስልጣንና ተግባራት

ኢትዮጵያ የብዝሀ ሕይወት ሀብቶችን ለመንከባከብ በብሔራዊ ደረጃ ግልጽ ፖሊሲ ቀርጻለች፡፡ የእጽዋት ጀነቲክ ሀብት ማዕከል (A Plant Genetics Resource Center) በሚል ለእጽዋት ብቻ ትኩረት ሰጥታ ስትሰራ ቆይታለች፡፡ ከ1998 እ.ኤ.አ ጀምሮ በእጽዋት ላይ ብቻ ሲሰራ የቆየውን የእጽዋት ጀነቲክ ሀብት ጥበቃ ለሁሉም ዓይነት ማለትም ለእጽዋት፣ እንስሳትና ደቂቅ አካላት እንዲጨምር ተደርጎ ዘላቂ ተጠቃሚነትና ተያያዥ የማህበረሰብ እውቀቶችን መጠበቅንም አካቷል፡፡ ስርዓተ ምህዳርም የትኩረት ማዕከል እንዲሆን ተደርጓል፡፡ የሀገሪቱን የብዝሀ ሕይወት ሀብቶች በዘላቂነት የመጠበቅና የማስተዋወቅ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ዓለም አቀፍና የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በማዳበር የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፡፡ አገሪቷ ለተቀበለቻቸው ብዝሀ ሕወትን የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ተጠሪ በመሆን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ይዋዋላል፡፡

ራዕይ

በ2022 በብዝሀ ሕይወት ጥበቃ እና ዘለቄታዊ አጠቃቀም በአፍሪካ የልህቀት ማዕከል መሆን

ተልዕኮ

የሀገራችን የብዝሀ ሕይወትና ተያያዥ ነባር ዕውቀቶችን በአግባቡ ማጥናት፣ አሳታፊ የጥበቃ ሥርዓትን መፍጠር፣ ማበልጸግ፣ አርክቦትና ጥቅም ተጋሪነትን በማረጋገጥ ሀብቱ በዘላቂነት ለልማት እንዲውል ማመቻቸት

ዓላማ

የአገሪቱ ብዝሀ ሕይወት ሀብትና ተያያዥ የማህበረሰቦች እዉቀት በአግባቡ መጠበቃቸዉንና በዘላቂነት ጥቅም ላይ መዋላቸዉን እንዲሁም እነዚህን በመጠቀም ከሚገኘዉ ጥቅም አገሪቷና ማህበረሰቦቿ ፍትሀዊና ሚዛናዊ ድርሻ ማግኘታቸዉን ማረጋገጥ ይሆናል።

ሁነቶች በፎቶ

National Ecosystem Trialogue Meeting
National Ecosystem Trialogue Meeting
Mapping Biodiversity Priorities Project Validation and Capacity Building Workshop
Mapping Biodiversity Priorities Project Validation and Capacity Building Workshop
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የ2013 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የ2013 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ
Conservation based field research activities of field crops at EBI
Conservation based field research activities of field crops at EBI
MBPPhaseIIExpertsMeetingSchedule

Mapping Biodiversity Priorities Phase II Experts Meeting

የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች የኮቪድ 19 ምርመራ አካሄዱ

የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች የኮቪድ 19 ምርመራ አካሄዱ

Six-National-Report-De-briefing-Meeting

Six National Report Debriefing Meeting

በኢንስቲትዩቱ ወርሃዊ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ

በኢንስቲትዩቱ ወርሃዊ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የ2013 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ውይይት
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የ2013 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አካሄዱ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አካሄዱ

previous arrowprevious arrow
next arrownext arrow

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አደረጃጀት

ኢንስቲትዩቱ ሰባት የምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች ያሉት ሲሆን እነርሱም፡- የእንስሳት ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ፣ የአዝዕርትና ሆርቲካልቸር ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ፣ የደንና ግጦሽ መሬት ዕፅዋት ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ፣ የጀነቲክ ሀብት አርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ፣ የደቂቅ አካላት ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ፣ የስልጠና፣ ማማከርና ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚ እና የማዕከላትና ዕፅዋት አፀዶች አስተባባሪ ናቸው። በተጨማሪም አስር የአስተዳደር ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚዎች ያሉት ሲሆን፣ እነርሱም፡- የመሠረታዊ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ፣ የሰው ሀብት አስተዳደርና ብቃት ሥራ አስፈጻሚ፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሥራ አስፈጻሚ፣ የተቋማዊ ለውጥ ሥራ አስፈጻሚ፣ የግዥና ፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ፣ የስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ፣ የኦዲት ሥራ አስፈጻሚ፣ የሥነ- ምግባርና የፀረ-ሙስና ሥራ አስፈጻሚ፣ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ኢንስቲትዩቱ 7 (ሰባት) የብዝሀ ሕይወት ማዕከላት መቱ፣ ሀዋሳ፣ ሀረር፣ መቀሌ፣ ጎባ፣ ባህርዳር እና አሶሳ ላይ አሉት፡፡ በተጨማሪም 2 (ሁለት) የዕጽዋት አጸዶች በሻሸመኔ እና ጂማ ሲኖሩት በፍቼ 1 (አንድ) የብዝሀ ሕይወት ጂን ባንክ አለው፡፡ ኢንስቲትዩቱ በዋና ዳይሬክተር እና በም/ዋ/ዳይሬክተር የሚመራ ሲሆን የስራ አመራር ኮሚቴው ሁሉንም ሥራ አስፈጻሚዎች አቅፎ አመራር ይሰጣል፡፡