You are currently viewing Ethiopian Biodiversity Institute conducted a summer volunteer program

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ-ግብር አከናወነ

የክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ-ግብሩ በጉራጌ ዞን፣ አበሽጌ ወረዳ፣ ማመዴ ቀበሌ በሚገኘው በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽ/ቤት በተገነባው የረገ ኤያት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የቤተ-መጻህፍት፣ የቤተ-ሙከራ እና ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ክፍሎችን የማደራጀት ስራ መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም ተከናውኗል፡፡

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ያሰባሰባቸው ንብረቶች የተቋሙ ኃላፊዎች፣ የት/ቤቱና የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የአካባቢው አስተዳደር አካላት በተገኙበት የድጋፍ ሥነ-ሥርዓቱ የተከናወነ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችን ምርቃት ጨምሮ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡

ድጋፉን በተመለከተ ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ ላደረገው ድጋፍ የምስጋናና ዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል፡፡

የተበረከቱትን ቁሳቁሶች አጠቃቀም በተመለከተ በት/ቤቱ ቤተ-ሙከራ እና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ክፍሎች አጭር ኦረንቴሽን ከተሰጠ በኋላ በክረምቱ የተተከሉ ችግኞች ሁኔታ በመጎብኘትና በቀጣይ ግንኙነት ላይ ሀሳብ በመለዋወጥ መርሀ ግብሩ ተጠናቋል፡፡