በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በአዲስ መልክ ባለማው ድረ-ገጽ ዙሪያ ለማኔጅመንት አባላት ማክሰኞ ጥቅምት 02 ቀን 2014 ዓ.ም ማብራሪያ ሰጠ፡፡
ማብራሪያውን አቶ ቴዎድሮስ ወርቁ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ባቀረቡበት ወቅት ድረ-ገጹን በአዲስ መልክ ማልማት ያስፈለገበትን ምክንያት፣ ያካተታቸውን ተጨማሪ ይዘቶችና ቋንቋዎች ወዘተ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ የማኔጅመንት አባላቱም ለተከናወነው ተግባር ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ለቀረቡ የማብራሪያ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ፕሮግራሙ መጠናቀቁን መረዳት ተችሏል፡፡


