You are currently viewing International Biodiversity Day was celebrated

ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ቀን በዓል ተከበረ

ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ቀን በዓል “ከስምምነት ወደ ተግባር፣ ብዝሀ ሕይወትን ወደ ቀድሞ ይዞታው መመለስ” በሚል መሪ ቃል ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተከበረ፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ኃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኢታ አማካሪ አቶ አንተነህ ፍቃዱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ፕሮግራም መልዕክት፣ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) መልዕክት እንዲሁም የዓለም አቀፉ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት ዋና ጸሀፊ የቪዲዮ መልዕክት ተላልፏል፡፡

በዓሉን የተመለከቱ ሰነዶች በፕሮፌሰር ሰብስቤ ደምሰው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ዶ/ር ሽፈራው ታደሰ የ(GGGI) ኢትዮጵያ ተወካይ፣ ፕሮፌሰር መኩሪያ አርጋው ከ (HoA-REC&N) እንዲሁም ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከፔለም ኢትዮጵያ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ውይይቱን የመሩ ሲሆን የብዝሀ ሕይወት ጉዳዮችን ያካተተ የብሔራዊ ሥርዓተ-ምህዳር ዳሰሳ ሰነድ በመዘጋጀቱ በቅርቡ ይፋ ተደርጎ ተግባራዊ እንደሚሆን ጠቁመዋል። በተጨማሪም የተለያዩ ማህበራዊ ዘር ባንክ ተወካይ አርሶ አደሮች ተሞክሮም ቀርቧል፡፡