በኢትዮጵያ ባዮስፌሮች ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሄደ Post author:በፍቃዱ ከፈለኝ Post published:June 21, 2023 Post category:Uncategorized በኢትዮጵያ በሚገኙት ባዮስፌሮች ዙሪያ ማክሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡የዬኔስኮ ፕሮግራም ልዩ ባለሙያ ዶ/ር ሳሙኤል ፓርቴይ የምክክር መድረኩን ዓላማና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል፡፡የሁሉም ባዮስፌሮች ሪፖርት፣ የሰውና ተፈጥሮ ብሔራዊ ኮሚቴ እንዲሁም የባዮስፌር ሪዘርቭ ኔትዎርክ ሰነዶች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠው የዕለቱ የምክክር መድረክ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡ ተጨማሪ ዜናዎች በ2014 ዓ.ም አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ውይይት ተደረገ December 10, 2021 በማህበረሰብ ዘር ባንክ ላይ ያተኮረ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ April 19, 2021 የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ August 14, 2023