በኢትዮጵያ ባዮስፌሮች ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሄደ Post author:በፍቃዱ ከፈለኝ Post published:ሰኔ 21, 2023 Post category:Uncategorized በኢትዮጵያ በሚገኙት ባዮስፌሮች ዙሪያ ማክሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡የዬኔስኮ ፕሮግራም ልዩ ባለሙያ ዶ/ር ሳሙኤል ፓርቴይ የምክክር መድረኩን ዓላማና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል፡፡የሁሉም ባዮስፌሮች ሪፖርት፣ የሰውና ተፈጥሮ ብሔራዊ ኮሚቴ እንዲሁም የባዮስፌር ሪዘርቭ ኔትዎርክ ሰነዶች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠው የዕለቱ የምክክር መድረክ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡ ተጨማሪ ዜናዎች ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ቀን በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ ተከበረ ሰኔ 13, 2022 የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ግምገማ መርሐ ግብር አከናወነ ሐምሌ 30, 2025 የጥብቅ ቦታዎች እንክብካቤ ማሻሻልና ማጠናከር ፕሮጀክት የመዝጊያ ወርክሾፕ ተካሄደ ህዳር 4, 2023