You are currently viewing The staff of the Ethiopian Biodiversity Institute visited the Gulele Botanical Center.

የኢትዮጵያ ብዝኃ ህይወት እንስቲትዩት ሠራተኞች የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከልን ጎበኙ ።

24ኛውን የዓለም ብዝኃ ህይወት ቀንን ተቋሙ በልዩ ልዩ መርኃ ግብሮች ሲያከብር “ከተፈጥሮ ጋር መስማማት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል የማኔጅመንት አካላትና ሠራተኞች በሙሉ የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከልን ለመጎብኘት በዐውዱ ላይ ተገኝተዋል።

 በዕለቱም የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ኃላፊና ሠራተኞች አቀባበል በማድረግ ቦታ ካስያዙ በኋላ የቱሪዝም ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መክብበ ማሞ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ያቀባበል ንግግር አድርገው ሃገር በቀል ችግኞች ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀው ለማስታወሻም በማኔጅመንት አካላት እንዲተከሉ ጋብዘዋል።

የኢትዮጵያ ብዝኃ ህይወት ኢንስቲቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዮት ብርሃኑ ለሰራተኞች መልዕክት ሲያስተላልፉ ሃገራችን በዘንድሮው የዓለም አቀፍ ብዝኃ ህይወት ቀን የተመረጠውን “ከተፈጥሮ ጋር መስማማት ለዘላቂ ልማት” ! በሚል መሪ ቃል ሃሳቡን አንግበን መነሳታችንን እና ግንዛቤ በመፍጠር ለውጥ ለማምጣት መዘጋጀታችንን በመግለፅ ሃገራችን ያላትን ሰፊ የብዝሀ ህይወት ሃብት ማጥናት ፣ መንከባከብና ጠብቀን ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባን አፅንዖት በመስጠት የበኩላችንን እንድንወጣ ማሳሰብ እወዳለሁ ።

አመሰግናለሁ ። ካሉ በኋላ ፡- ሠራተኞች ሁላችንም ቀደም ብለው የተተከሉትን በመጎብኘትና በማየት መንከባከብ፣ ውሃ ማጠጣት፤ ማረምና ያልፀዱትን በማንሳት ሥራ በመሳተፍ በጋራ እናክብር ! በማለት ማስታወሻ ችግኞችን ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በማዕከሉ ተክለዋል።