You are currently viewing The green legacy program was implemented

የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ተከናወነ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል አካል የሆነውን አረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ሀምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም አከናወነ፡፡

ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር መርሀ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሶስት ሚሊዮን ሀገር በቀል ችግኞች በኢንስቲትዩቱ መዘጋጀታቸውን አስታውሰው መላው ሰራተኞች በመሳተፋቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡.

የደን እና ግጦሽ መሬት ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አበራ ስዩም በበኩላቸው ሀገር በቀል ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት መንከባከብ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞችም በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል አካል የሆነውን አሻራቸውን በማኖራቸው ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡