የድህረ 2020 ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ማዕቀፍ ተግባሪ ግብረ-ኃይል ቅዳሜ መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ፒራሚድ ሆቴል ውይይት አደረገ፡፡
ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አጠቃላይ የድህረ 2020 ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ማዕቀፍ ዝርዝር መረጃዎችን ያካተተ ሰነድ አቅርበዋል፡፡
ዶ/ር ምስክር ተሰማ የ Early Action Service (EAS) ፕሮጀክት አስተባባሪ የዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ማዕቀፍ ዓላማዎች፣ አካላት እና ውጤቶችን የተመለከተ ሰነድ ለውይይት አቅርበዋል፡፡ ውይይቱን ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር የመሩት ሲሆን ከግብረ-ኃይሉ አባላት የተለያዩ ሀሳቦች፣አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡
ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሾች የተሰጡ ሲሆን ግብረ-ኃይሉ የዓለም አቀፉ የድህረ 2020 የብዝሀ ሕይወት ዕቅድ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተዘጋጁ መመሪያዎችና ቅጾች መሰረት ለማዘጋጀትና ሪፖርት ለማድረግ ዝግጁነቱን አረጋግጧል፡፡
