የጋራ ሴሚናሩ በኢትዮጵያ የብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት እና በአለም አቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት መካከል “Biodiversity resources for agriculture and food systems transformation-challenges and opportunities for sustainability” በሚል መሪ ቃል ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ።
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል።
በሴሚናሩ ላይ የአለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር Prof. Appolinaire Djikeng, Director General, International Livestock Research Institute (ILRI) እና የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማርዮ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማርዮ “Ethiopian’s Biodiversity landscape”, የተሰኘ ሰነድ ሲያቀርቡ “The role of Genebanks for agriculture and food systems transformation” በዓለም አቀፉ የእንሰሳት ምርምር ተቋም የዘረመል ባንክ ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ ተሬሳ እና “Ethiopian’s food systems transformation landscape” presented by Dr. Namukolo Covic, ILRI Director General’s Representative to Ethiopia and CGIAR Country Convenor for Ethiopia ቀርቧል፡፡
የፓናል ውይይት በዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር፣ ዶ/ር አለማየሁ ተሬሳ በዓለም አቀፉ የእንሰሳት ምርምር ተቋም የዘረመል ባንክ ዳይሬክተር እና ዶ/ር ተስፉ ፈከንሳ በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የእንስሳት ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ተደርጓል፡፡
ሴሚናሩን የተመለከቱ ሀሳቦች በዶ/ር አብዮት ብርሃኑ በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የጀነቲክ ሀብት አርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት ምርምር መሪ ሥራ አስፈፃሚ፣ ዶ/ር ገመዶ ዳሌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና Dr. Andre Van Rooyen, Principal Scientist and ICRISAT Country Representative to Ethiopia ቀርበዋል።
የመግባቢያ ሰነድ በዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ የብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና Dr. Namukolo Covic, ILRI Director General’s Representative to Ethiopia and CGIAR Country Convenor for Ethiopia ተፈራርመዋል።
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማርዮ የመዝጊያ ንግግር አድርገው ሴሚናሩ ተጠናቋል።

