You are currently viewing Biodiversity and Ecosystem Service Network (BES Net) draft document was presented

ብዝሀ ሕይወትና የስነ-ምህዳር አገልግሎት Biodiversity and Ecosystem Service Network (BES Net) ረቂቅ ሰነድ ቀረበ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት BES NET ፕሮጀክት ረቂቅ ሰነድ ላይ በቢሾፍቱ ፒራሚድ ሆቴል ዓርብ ታህሳስ 26 ቀን 2016ዓ.ም ግምገማ ተደረገ፡፡

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማርዮ መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለፁት የBES NET ፕሮጀክት ለሀገር ትልቅ ፋይዳ ያለዉ በመሆኑ ስራዉን ሲሰሩ ለነበሩ ግብረ ሀይሎች የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አክለዉም ይህ ጥናት ከተጀመረ አጭር ግዜ ቢሆንም የፕሮጀክቱን ረቂቅ ሰነድ ለግምገማ እንዲቀርብ ጊዜያቸዉንና እዉቀታቸዉን በማፍሰስ በቁርጠኝነት ለተሰራዉ ስራ አድናቆታቸዉን አቅርበዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ እንደገለፁት ይህን ረቂቅ ሰነድ የተለያዩ ተቋማትን የተሳተፉበት ሲሆን ጥናቱን ለመስራት ቅድመ ዝግጅት ከተካሄደ በኋላ መረጃ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተሰባሰበ መሆኑና ረቂቅ ሰነዱ በተገቢ ትኩረት ተዘጋጅቶ ለግምገማ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡

Assessment team on matters related to “Biodiversity and Ecosystem Service (BES) “The National Biodiversity Platform- Ethiopia”, “Outputs of the National Ecosystem (NEA) & Development of outreach Materials” በመድረኩም በሶስት ዋና ዋና ሀሳቦችና በሶስት ንዑሳን ሀሳቦች ተከፋፍሎ የቀረበ ሰነድ ሲሆን በርካታ ሀሳቦች እንደ ግብዓት ቀርበዉ ግምገማና አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡