You are currently viewing New Directors were appointed

ከአዳዲስ አመራሮች ጋር ትውውቅ ተደረገ

ለኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዶ/ር ካርታ ካስኬ በዋና ዳይሬክተርነት እንዲሁም ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ በም/ዋና ዳይሬክተርነት የተሾሙ ሲሆን መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከማኔጅመንት አባላት ጋር ትዉዉቅ አድርገዋል፡፡

የቀድሞ የኢንስቲትዩቱ አመራሮች ዶ/ር መለሰ ማርዮ እና ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የተከናወኑ ስኬቶችን አስታውሰው፤ የተጀመሩና ሊጠናቀቁ የሚገባቸውን ተግባራት ለአዳዲሶቹ አመራሮችና ለማኔጅመንት አባላት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ለነበራቸው ቆይታም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

አዳዲሶቹ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላትም የተጀመሩና ሊጠናቀቁ የሚገባቸውን ተግባራት ለማጠናቀቅ እንዲሁም ኢንስቲትዩቱ ለሀገራችን እድገትና ብልጽግና የሚያበረክተዉን ቁልፍ ሚና ለማሳደግ በትጋት የሚሠሩ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።

ዶ/ር ካርታ ካስኬ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በዳይሬክተርነት፣ ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ ደግሞ በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በመሪ ሥራ አስፈፃሚነት ሲሰሩ መቆየታቸዉ ይታወሳል።