የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ግምገማ መርሐ ግብር ከሀምሌ 22-23 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አከናወነ፡፡
ዶ/ር ሳምሶን ሺመልስ የስልጠና፣ ማማከርና ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚ መርኃ ግብሩን በማዘጋጀት እና በማስተባበር ተቋማችን ልማታዊ፣ የለውጥና ተጨባጭ ውጤት አካል እንዲሆን የታለመ መሆኑን በአፅንዖት ገልፀው የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ ዶክተር አብዮት ብርሃኑን የተቋሙን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጋብዘዋል።
ዶክተር አብዮት ብርሃኑም እንኳን ለዚህ ዓመታዊ የምርምር ( Flage Ship Project ) መርኃ ግብር አደረሰን እያልኩ ተቋማችን ብዙ ተመራማሪዎች እንዳሉት ይታወቃል፤ ለቀጣይ ዓመት ተቋሙን እንደ ስሙ የምርምር ተቋም ለማድረግ ታስቦበት የሚሰራ፤ የወደፊቱን ሥራ ለማመላከት በተለመደ ልማዳዊ አካሄድ ላለመሄድ ሃብትንና ሰውን ከፍ ወዳለ እውቀትና ሥነ-ምግባር ለማምጣት፤
አሰራሩንም ዘመኑ ወደ ደረሰበት የቴክኖሎጂ ደረጃ በማድረስ የተቋሙን ዓላማና ግብ ማሳካት፤ _ የህብረተሰቡን ችግር መፍታት፤ -ጥቅሙን ማስከበርና ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ፤ ዓላማ ያደረገ መርኃ ግብር ነው።
የመጀመሪያው « ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖር » ሲሆን ተመራማሪዎቻችንና የምርምር ውጤቶቻችን ከፍተኛ አዎንታዊ ተፅዕኖ ማምጣት አለባቸው፤ / Disciplinary Holistic / መሆን አለባቸው፤ ይህን የውጤት ታሪክ ምልክታችን ማድረግ አለብን ፤ የምንከተለው የምርምር መርኃችን ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ የሚከተለውን ዲሲፒሊን በመከተል ነው። ካሉ በኋላ በውይይት የምናዳብረው ስለሆነ ወደ መርኃ ግብራችን በቀጥታ እንግባ ፤ በማለት በይፋ ውይይቱን ከፍተዋል።
ዶክተር ካርታ ካስኬ ከነበረባቸው አስቸኳይ ሥራ በመድረሳቸው የፕሮግራሙ አስተባባሪ ዶክተር ሳምሶን ሺመልስ በመርኃ ግብሩ ጭብጥ መልዕክት እንዲያስተላልፉና አቅጣጫ እንዲሰጡ ጋብዘዋል። ዶክተር ካርታ ካስኬ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር የምርምርን አስፈላጊነት ከተቋማችን ዋና ዓላማ ጋር ለተጨባጭ ውጤትና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚሰጥ ፤የሚቆጠር መሬት ላይ ወርዶ ለህብረተሰብ የሚታይ እንዲሆን ማቀድና መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
ባለው የሰው ኃይል ሙሉ አቅም በመሥራት የብዝሀ ህይወትን ጠቀሜታዊ ሚና ማላቅ ከምሁራን ተመራማሪዎች ይጠበቃል ሲሉ ሙያዊ ጥልቀት ያላቸው የትኩረት ነጥቦች አንስተው በሚቀርቡት የምርምር ሥራ ፕሮጀክት ግምገማ መመዘኛ ነጥቦችንም አቅጣጫዎች አመላክተዋል።
በመርኃ ግብሩ መሠረት ተመራማሪዎች ፕሮጀክታቸውን ለሁለት ቀናት በተከታታይ አቅርበው በያንዳንዳቸው ላይ አስተያየት ማብራሪያና ማሻሻያ ሃሳቦች ተሰጥቶባቸው በጥራት ተጠናቀው እንዲቀርቡ በዶክተር ሳምሶን ሺመልስ ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ገልፀው ዶክተር ካርታ የጥናትና ምርምር ሥራ የሚጠይቀውን መርህና መስፈርት ጠብቆ ውጤት ማስመዝገብ ሥራችንና ዓላማችን ሆኖ ባቀረባችሁት ተግዳሮት በድጋፍ ሰጪ ክፍሎች የሚያጋጥሙ የአፈፃፀም ችግሮች ልማዳዊነት እንዲቀር በግልፅ እየተናበብንና ቴክኖሎጂን በመጠቀም እየፈታን እያስተካከልን ብዝሀ ሕይወትን ከህዝብ እና ከመንግሥት አቀራርበን በውጤት ደግሞ ሃገራችንን እናበለፅጋለን ። ሲሉ መርኃ ግብሩን አጠቃለዋል።
