You are currently viewing Database application end users training was given for EBI staffs

ዘመናዊ የሆነ የመረጃ ቋት (ዳታቤዝ) አጠቃቀም ስልጠና ተሰጠ

የአዝዕርትና ሆርቲካልቸር ብዝሀ ሕይወት ዳይሬክቶሬት የዘር ብቅለት መረጃን ለመመዝገብ ሲጠቀምበት የነበረዉን መረጃ ለማዘመን ይረዳ ዘንድ በዘመናዊ መልኩ የተሟላ መረጃን መስጠት የሚያስችል የዳታቤዝ ማልማት ስራ ተጠናቆ ለክፍሉ ባለሞያች ስልጠና ተሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ወርቁ ዳታቤዝ ማልማት ያስፈለገበት ዋና ምክንያት የቀድሞዉ የመረጃ አያያዝ ስርዓት በቂ ባለመሆኑ የተፈለገውን ያህል መረጃ ባለሟሟላቱ አዲስና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ለመዘርጋት እንዲቻል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ጥራት ያላቸዉ መረጃዎችን ለማግኘት፣ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ሀላፊዎች መረጃዉን በቀላሉ ለመቆጣጠር እንዲያመቻቸዉ ከማስቻል ባሻገር የዘር ብቅለት መጠናቸዉ ምን ያህል እንደሆነና ምን ያህል መረጃ መሰብሰብ እንደተቻለ የሚያሳይ ዘመናዊ የሆነ ስርዓት እንደተዘረጋ አሰልጣኙ በስልጠናው ወቅት ተናግረዋል፡፡