በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የምርምር፣ ስርጸትና ፕሮጀክት ትግበራ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት የሚዘጋጀው ወርሀዊ ሳይንሳዊ ሴሚናር ህዳር 08 ቀን 2014 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ ተካሄደ፡፡
ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር በትምህርት ሚኒስቴር የሳይንስና ምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል Current Issues and Global Trends in Scientific Integrity: Facts and Recommendations for EBI Researchers በተሰኘ ርዕስ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ ከኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ከቀረቡ በኋላ እንደ ተቋም ጥራቱን የጠበቀ ጆርናል ለማሳተም መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
ዶ/ር መለሰ ማሪዮ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በቀጣይ ጆርናሎች ለህትመት ከመላካቸው በፊት የየዳይሬክቶሬቶቹ ኃላፊዎች እንዲሁም የምርምር፣ ስርጸትና ፕሮጀክት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ሊያውቀው እንደሚገባ ያስታወሱ ሲሆን በምርምር፣ ስርጸትና ፕሮጀክት ትግበራ ዳይሬክቶሬት መመሪያ ሊዘጋጅ እንደሚገባ አስታውሰው ወርሀዊ ሴሚናሩ ተጠናቋል፡፡