You are currently viewing Forum for policymakers, researchers, and practitioners Held

የአጋር የምርምር ተቋማትና የቁልፍ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሄደ

የአጋር የምርምር ተቋማትና የቁልፍ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ፒራሚድ ሆቴል ተካሄደ፡፡

የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ያደረጉ ሲሆን Dr. China Williams እና Dr. James Borell ከ Royal Botanic Gardens,KEW በመድረኩ ላይ ሀሳባቸውን አቅርበዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሰብስቤ ደምሰው ከአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ Progress towards identifying Tropical Important Plant Areas in Ethiopia የተሰኘ ሰነድ ሲያቀርቡ Dr. James Borell ከ Royal Botanic Gardens,KEW Identifying hotspots of agrobiodiversity in Ethiopia-unifying wild and agricultural biodiversity conservation የተሰኘ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

Payments for Agrobiodiversity Conservation-services as a mechanism to fund agrobiodiversity zones የተሰኘ ሰነድ ወጣት ቤዛዊት ገናናው ሲያቀርቡ Opportunities to use OECM to support Ethiopia working towards the 30X30 GBF Target የተሰኘ ሰነድ በ Dr. China Williams እና Miss Sophie Jago እንዲሁም Celebrating completion of Red Listing all of Ethiopia’s endemic flora የተሰኘ ሰነድ ፕሮፌሰር ስለሺ ነሞምሳ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አቅርበዋል፡፡

የቡድን ውይይት ተደርጎ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር የብዝሀ ሕይወት ሀብቶችን ለማበልጸግ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም ሀብት ማሰባሰብ እንደሚገባ ጠቁመው ፖሊሲ አውጪዎች፣ የምርምሩ ማህበረሰብ እና ተግባሪዎች በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡