You are currently viewing A memorandum of understanding was signed

የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ተቋማት ጋር ሰኔ 01 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ሰነዱን የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ከAlabaster International፣ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና ከ Jomo Kenyatta University of Agriculture and Technology ጋር በእንሰት የጀነቲክ ሀብት ምርታማነትና አጠቃቀም ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ፕሮቶኮልን መሰረት በማድረግ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

በመግባቢያ ሰነዱ ላይ ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እንሰትን ከባህላዊ አዘገጃጀት ይልቅ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አጠቃቀሙን ማሻሻል እንደሚገባ የጠቆሙ ሲሆን ዶ/ር በሀይሉ መርደኪዮስ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ኅ/ሰብ ተሳትፎ ም/ፕሬዘዳንት እንዲሁም ሻነን ፈርናንዶ የ Alabaster International መስራችና ፕሬዘዳንት ከኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ መስራት መቻላቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡