You are currently viewing 700 million seedlings were planted in one night for the “Renewal through Planting” initiative

700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር_ " በመትከል ማንሰራራት "

ዛሬ ማለዳ ሀምሌ 24/11/2017 ዓ/ም ደማቅ አሻራችንን ያሳረፍንበት ቀን ነው ። የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች በሸገር ክፍለ ከተማ በቱሉዲምቱ አካባቢ ተገኝተዉ አረንጓዴ አሻራቸዉን አሳርፈዋል ። ከችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሩ አስቀድሞ አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ ካርታ ካስኬ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የሸገር ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩቱ በቱሉዲምቱ አካባቢ የተረከበዉ ቦታ የተጎዳ መሬት በመሆኑ ከችግኝ ተከላዉ ባሻገር መሬቱ በቶሎ እንዲያገግም መሰራት እንዳለበት ተነግሯል ። ሰባት ዓይነት አምስት ሺ ሀገር በቀል ችግኞች አልቢዝያ ፣ አኬዢያ ፣ ኮርዲያ ፣ ከበርጂያ ፣ ሚሊቲያ ፣ኦሊያ እና ፕሩነስ በቦታው ተተክለዋል።

ተቋሙ በሶስት ዙር 12ሺ ሀገር በቀል ችግኞችና በማዕከላትም በርካታ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራን በደማቁ ለማሳረፍ ተችሏል ። ለዚህም ሰራተኛዉ ላሳየዉ ትጉህ ተሳትፎ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አመራሮች አመስግነዋል ።