You are currently viewing The doubling of the number of HIV-positive patients is said to be a cause for concern

በኤች.አይ.ቪ የሚያዙ ህመምተኞች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩ አሳሳቢ ነዉ ተባለ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ህዳር 22 በዓለም አቀፍ ደረጃ ተከብሮ የሚውለዉን የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቀንን አስመልክቶ በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ ለሰራተኞች ስለ በሽታዉ ስልጠና ሰጠ፡፡

ኤች.አይ.ቪ ኤድስ 1989ዓ.ም ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ መጀመሪያ ከገባበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸዉን ወገኖቻችንን ህይወት ቀጥፏል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ህብረተሰቡ ለበሽታዉ እየሰጠዉ ያለዉ ግምት እያነሰ በመምጣቱ በበሽታው እየተያዘ ያለዉ የሰዉ ቁጥር በእጥፍ እየጨመረ መምጣቱን በአዲስ አበባ ተስፋ ጎህ የህብረተሰብ ጤና ባለሙያ አቶ ያሬድ ቦጋለ ስልጠዉን በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡ የጫት፣ የአደንዛዥ አፅ እና የአልኮል መጠጥ ተጠቃሚ የማህበረሰብ ክፍል መብዛቱና ይህም ለልቅ የግብረስጋ ግንኙነት የሚዳርግ መሆኑ ህብረተሰቡ በኤች አይ ቪ እንዲጠቁ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ባለሙያዉ ገልፀዋል፡፡

የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ህመምኞችና ሟቾች ቁጥር መጨመር የሰዎች አማካይ እድሜ በማሳጠር የአምራች ህዝብ ቁጥር የሚቀንስ በመሆኑ በሀገር ላይ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን እንደሚያስከትል በመድረኩ ተጠቅሷል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎችም በሽታዉ መረሳቱን በተመለከተና በፍጥነት እየተስፋፋ ከመምጣቱ አኳያ ከመንግስት፣ ከህበረተሰቡ፣ ከጤና ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸዉ አካላት ምን ይጠበቃል የሚሉ ሀሳቦችን በማንሳት በመድረኩ ውይይት አድርገዋል፡፡