የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የ2025-2030 የኢትዮጵያ ብሄራዊ የብዝሀ ህይወት ስትራቴጂ እና የድርጊት መርሃ ግብር (NBSAP) ሰነድን በአፍሪካ የአየር ንብረት መድረክ ላይ አቀረበ።
ሰነዱ በ19 ልዩ ኢላማዎች ዙሪያ የተዋቀረ፣ በ124 ዝርዝር ተግባራት የተደገፈ እና በ88 አመላካቾች የተዘጋጀ አጠቃላይ የስድስት አመት ስትራቴጂክ ማዕቀፍ ነው። ትግበራው በመስከረም 2018 ዓ.ም መጨረሻ ላይ በይፋ ይጀምራል።
