You are currently viewing Planning Coordination Meeting Held

የዕቅድ ትስስር ተከናወነ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ከማዕከላት አስተባባሪዎች ጋር የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ትስስር ከነሀሴ 19-20 ቀን 2018 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አከናወነ፡፡

አቶ ግሩም ፋሪስ የማዕከላትና እጽዋት አጸድ አስተባባሪ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው የመድረኩን ዓላማ አስተዋውቀዋል፡፡

ዶ/ር አብዮት ብርሀኑ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሪፎርሙ ማዕከላትን በሚጠቅም መልኩ እንደሚከናወንና ፕሮጀክቶች ከነበጀታቸው ወደ ማዕከላት እንደሚወርዱ ጠቅሰው “አንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት” የሚለውን መርህ መሰረት በማድረግ መስራት እንደሚገባ አስታውሰዋል፡፡

በተጨማሪም ማዕከላት ጠንካራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸውና በማዕከላት መካከል ውድድሮች እንደሚከናወኑም ጭምር ገልጸዋል፡፡

አቶ ማስረሻ የማነ በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ዕቅድን በጀትን ታሳቢ አድርገው አቅርበዋል፡፡ አያይዘውም የማዕከላትና ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ትስስር አስፈላጊነትን ዘርዝረው የማዕከላት እንቅስቃሴና ተግባራት ለዋናው ውጤት መጋቢ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች ከማዕከላት ጋር በጋራ የሚሰሯቸውን ተግባራትና ውጤቶች በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የማጠቃለያ ሀሳቦችና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች በዶ/ር ካርታ ካስኬ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና ዶ/ር አብዮት ብርሀኑ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ተሰጥተው የዕቅድ ማስተሳሰሩ መርሀ-ግብር ተጠናቋል፡፡