የመሪ ሥራ አስፈጻሚ ክፍሉ ዓላማ
የእንስሳት ብዝሀ ሕይወት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዓላማ ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሀገሪቱ ያላትን የእንስሳት ተለያይነት የማጥናት፣ በዘቦታ እና በኢዘቦታ የመጠበቅ እና በዘላቂነት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረግ ተግባራትን ማከናወን ነው፡፡
የእንስሳት ብዝሀ ሕይወት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዓላማ ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሀገሪቱ ያላትን የእንስሳት ተለያይነት የማጥናት፣ በዘቦታ እና በኢዘቦታ የመጠበቅ እና በዘላቂነት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረግ ተግባራትን ማከናወን ነው፡፡
የእንስሳት ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ የሚያከናውናቸውን የዘቦታና ኢዘቦታ ማንበር እና የዘለቄታዊ አጠቃቀም ተግባራት እንዲሁም እነዚህን አበይት ተግባራት ለማከናወን የሚያግዙ የጥናትና ምርምር ሥራዎቹን በላቀ ደረጃ ለመፈጻም በለማዳ፣ በዱርና በውሀ ውስጥ እንስሳት ብዝሀ ሕይወት ዘርፎች ተደርጅቶ ሥራዎቹን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ አደረጃጀቶች እስከ ማዕከል ደረጃ የወረዱ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የተሟላ ባይሆንም ከ60 በላይ የዘርፉ ተመራማሪዎችን ሊይዝ እንደሚችል ተደርጎ የተቀረጸ ነው፡፡ በአሁኑ ደረጃ በሥራ ላይ ያሉ 42 ተመራማሪዎች የዘርፉን ሥራ በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡