በዓመት ሁለት ጊዜ በድህረ-ገፅ እና በህትመት የሚቀርቡ መፅሄቶችን እናዘጋጃለን፡፡ የመፅሄቱ ጽሑፎችና ዜናዎች የሚያተኩሩት በሳይንሳዊ እውነታዎች እና አሃዞች ላይ በአብዛኛው በብዝሀ ሕይወት ጥበቃ ፣ ዘላቂ አጠቃቀም አርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት (ABS) ላይ ነው። በተጨማሪም ለህትመት ከታሰቡት ጽሑፎች መካከል ከአካባቢ ጥበቃ ፣ ከግብርና ምርምር ፣ ከአሳ እና ከባዮቴክኖሎጂ አካባቢዎች ይገኙበታል።

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የዜና መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 1

ርዕሰ-ጉዳዮች፡-

  • የብዝሀ ሕይወት ዜና
  • የጤፍ የጀነቲክ ሀብት አርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት ምቹ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች (ገመዶ ዳሌ)
  • የብዝሀ ሕይወትና ሥርዓተ ምህዳር ጉዳይ ለምን ያሳስበናል? (ጌታቸው ተስፋዬ)
  • የብዝሀ ሕይወት አሳሳቢ ጉዳዮች፣ ችግሮችና ተስፋዎች (ጌታቸው ተስፋዬ)
  • የዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት CBD አተገባበር በኢትዮጵያ
  • የደን ጀነቲክ ሀብት ጥበቃና ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ
  •  የሥርዓተ ምህዳር ጉዳዮችን ማስረጽ/ማካተት
  • በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የከረዩ አርብቶ አደሮች የሚጠቀሙባቸው አንዳንድ የባህላዊ ሕክምና እፅዋት(ከቡ ባለሚ)
  • በማዕከላዊ እና በሰሜን ኢትዮጵያ ጀርምፕላስምን የመሰብሰብ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ፣ የመሬት አጠቃቀም ለውጦች እና የጄኔቲክ መሸርሸር
  • ኢትዮጵያ ያልተጠቀመችባቸው የባህላዊ የመድኃኒት ዕፅዋት ብሔራዊ ኢኮኖሚያዊ እሴቶች
  • የዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት CBD ስትራቴጂክ ዕቅድ 2011-2020
  •  የጀኔቲክ ሀብትና የማህበረሰብ ዕውቀት አርክቦት
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የዜና መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 1

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የዜና መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 2 

ርዕሰ-ጉዳዮች፡-

  • የማይክሮቦች እና የማይክሮባዊ ተጽዕኖ መረዳት
  • በኢትዮጵያ የብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ባህላዊ የማይክሮባዊ ናሙና አሰባሰብ ሁኔታ
  • የእንጉዳይ ልማት ለዘላቂ የምግብ ዋስትና
  • በሜታጅኖሚክስ ደቂቅ አካላት ተለያይነተት ትንተና ውስጥ መሰረታዊ የአሰራር ስርዓት ለውጥ
  • አልጌ ለሥነ -ምህዳራችን ያላቸውን ሚና በጭራሽ አይናቁ
  • ደቂቅ አካላት፡ የባዮቴክኖሎጂ ምቹ መሣሪያዎች
  • መጤ ወራሪ ዝርያዎች በቦረና ዞን የአርብቶ አደር አካባቢ ማህበረሰብ የግጦሽ እና በግጦሽ የጄኔቲክ ሀብት ተለያይነት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ
  • በሰሜን ሸዋ ለቀድሞው በመስክ ከሚገኙ ነባር የአርሶ አደሩ የሰብል ዝርያዎች የተሰበሰቡ ናሙናዎችን መረጃ ማደራጀት
  • ሕገወጥ የጀኔቲክ ሀብቶች ዝውውር በኢትዮጵያ፣ ከባለድርሻ አካላት ዕውቀት አንጻር የመጀመሪያ ደረጃ የዳሰሳ ጥናት
  • የብዝሀ ሕይወት ዜና
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የዜና መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 2

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የዜና መጽሔት ቁጥር 3

በቀጣይ የዜና መጽሔት ቁጥር 3 በታህሳስ 2014 ለማዘጋጀት በሂደት ላይ እንገኛለን፡፡ አርቲክሎችን እየሰበሰብን ስለሆነ በኢ-ሜይል አድራሻችን info@ebi.gov.et መላክ ትችላላችሁ፡፡

መመሪያዎች፡-

  • ርዕሰ-ጉዳዮች፡- የብዝሀ ሕይወት አርክቦት ፣ ዘላቂ ጥቅምና ጥቅም ተጋሪነት ፣ ግብርና ፣ አካባቢ ፣ የዓሳ ዕርባታና ባዮቴክኖሎጂ
  • የገጽ ብዛት፡- ከ5 ገጥ ያልበለጠ ፣ በ1.5 ስፔስ ፣ Times New Roman
  • ይዘት፡- መነሻ ፣ የጥናት ዘዴ ፣ ትንተና ፣ ማጠቃለያ ፣ ማጣቀሻዎች