በብሔራዊ ሥነ ምህዳር ፕሮጀክት ዳሰሳ ዙሪያ ውይይት ተካሔደ Post author:ፍሬህይወት ብርሀኑ Post published:ግንቦት 3, 2021 Post category:Uncategorized በብሔራዊ ሥነ ምህዳር ፕሮጀክት ዳሰሳ ዙሪያ ውይይት ተካሔደበብሔራዊ ሥነ ምህዳር ፕሮጀክት ዳሰሳ ዙሪያ ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ውይይት ተካሄደ።በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ / ር መለሰ ማሪዮ የሥነ ምህዳር ዳሰሳ ለመረጃ ፈላጊዎች ምላሽ የሚሰጡ ፣ ስህተቶችን የሚቀንሱ፣ የወደፊቱን አቅጣጫዎች በማሳየት ለውሳኔ እንደሚረዳ ጠቅሰዋል።የውይይት መድረኩ ዓላማም በሥነ-ምህዳሮች ዙሪያ እውቀትን በማካፈል ግንዛቤን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።ከብሔራዊ ሥነ -ምህዳራዊ ዳሰሳ የተገኘው መረጃ በሥነ-ምህዳሮች ዙሪያ፣ ስጋቶችን በመለየት፣ እሴቶችን በመረዳት እና አጠቃላይ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመገምገም ይረዳናል ብለዋል።አያይዘውም በሥነ -ምህዳር ሥርዓቶች ምደባ ላይ አስተዋፅኦ በማበርከት ረገድ ምሁራን ሚና እንዳላቸው አስታውሰዋል።በስብሰባው ላይ ገለጻዎች ቀርበው ውይይቶችም ተካሂደዋል።የብሔራዊ ሥነ ምህዳር ዳሰሳ ፕሮጀክት ብሔራዊ ሥነ ምህዳራዊ ግምገማዎችን ለማካሄድ እና የግምገማዎችን ውጤት ለውሳኔ አሰጣጥ እንዲረዳ በአገር ደረጃ የተቋቋመ ፕሮጀክት ነው። ተጨማሪ ዜናዎች በኤች.አይ.ቪ የሚያዙ ህመምተኞች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩ አሳሳቢ ነዉ ተባለ ታህሳስ 28, 2021 የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ተከናወነ ሐምሌ 11, 2023 ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ቀን በዓል ተከበረ ግንቦት 23, 2023