በብሔራዊ ሥነ ምህዳር ፕሮጀክት ዳሰሳ ዙሪያ ውይይት ተካሔደ Post author:ፍሬህይወት ብርሀኑ Post published:ግንቦት 3, 2021 Post category:Uncategorized በብሔራዊ ሥነ ምህዳር ፕሮጀክት ዳሰሳ ዙሪያ ውይይት ተካሔደበብሔራዊ ሥነ ምህዳር ፕሮጀክት ዳሰሳ ዙሪያ ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ውይይት ተካሄደ።በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ / ር መለሰ ማሪዮ የሥነ ምህዳር ዳሰሳ ለመረጃ ፈላጊዎች ምላሽ የሚሰጡ ፣ ስህተቶችን የሚቀንሱ፣ የወደፊቱን አቅጣጫዎች በማሳየት ለውሳኔ እንደሚረዳ ጠቅሰዋል።የውይይት መድረኩ ዓላማም በሥነ-ምህዳሮች ዙሪያ እውቀትን በማካፈል ግንዛቤን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።ከብሔራዊ ሥነ -ምህዳራዊ ዳሰሳ የተገኘው መረጃ በሥነ-ምህዳሮች ዙሪያ፣ ስጋቶችን በመለየት፣ እሴቶችን በመረዳት እና አጠቃላይ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመገምገም ይረዳናል ብለዋል።አያይዘውም በሥነ -ምህዳር ሥርዓቶች ምደባ ላይ አስተዋፅኦ በማበርከት ረገድ ምሁራን ሚና እንዳላቸው አስታውሰዋል።በስብሰባው ላይ ገለጻዎች ቀርበው ውይይቶችም ተካሂደዋል።የብሔራዊ ሥነ ምህዳር ዳሰሳ ፕሮጀክት ብሔራዊ ሥነ ምህዳራዊ ግምገማዎችን ለማካሄድ እና የግምገማዎችን ውጤት ለውሳኔ አሰጣጥ እንዲረዳ በአገር ደረጃ የተቋቋመ ፕሮጀክት ነው። ተጨማሪ ዜናዎች በአሳታፊ የነባር ዘር ምርምር (Participatory Variety Selection) የተገኙ ነባር የስንዴ ዓይነቴዎች (farmers varieties) በምርምር ጣቢያ የመዝራት መርሀ-ግብር ተከናወነ ሚያዝያ 14, 2025 የአጋር የምርምር ተቋማትና የቁልፍ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሄደ መጋቢት 19, 2024 የብሔራዊ ብዝሀ ሕይወት መድረክ ዉይይት ተካሄደ ጥር 11, 2024
በአሳታፊ የነባር ዘር ምርምር (Participatory Variety Selection) የተገኙ ነባር የስንዴ ዓይነቴዎች (farmers varieties) በምርምር ጣቢያ የመዝራት መርሀ-ግብር ተከናወነ ሚያዝያ 14, 2025