You are currently viewing A national project string committee meeting was held

ብሔራዊ የፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ ተደረገ

ብሔራዊ የድህረ-2020 የብዝሀ ሕይወት ማዕቀፍ ቅድመ-ትግበራ ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም በቢሾፍቱ ፒራሚድ ሆቴልና ሪዞርት ተደረገ፡፡

የእንኳን ደህና መጣቸሁ መልዕክት ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ያስተላለፉ ሲሆን ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር “Processes and Outcomes of the post-2020 GBF” የተሰኘ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

በመቀጠልም “GEF Enabling Activity: GBF Early Action Support Project: Modalities of Implementation” ሰነድ በፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ምስክር ተሰማ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የውይይት መድረኩን ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር የመሩት ሲሆን ከተሳታፊዎች ገንቢ ሀሳቦች ተሰብስበው ውይይቱ መጠናቀቁን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ዘግቧል፡፡