የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ህዳር 1 ቀን 2014ዓ.ም ከኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ዙሪያ ዉይይት አካሄዷል፡፡
የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና የመንግስት ሰራተኞች ሚና የሚል ወቅቱን የሚገልፅ ሰነድ አቅርበዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ በርከት ያሉ ሀሳቦች በተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ሀገራዊ ተልዕኮን የሚወጣውን፣ የእንስሳትና ዕጽዋት ዘር ዋስትና፣ የደቂቅ አካላትን ሀብቶች ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍን የሚያረጋግጥ ትልቅ ተቋም በመሆኑ በአግባቡ ሊጠብቁት እንደሚገባ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማርዮ ገልፀዋል፡፡
ከተሳሳቱ የመረጃ ምንጮች ራሳችንንም ሆነ ሀገራችንን በመጠበቅ ሀላፊነታችንን መወጣት ተገቢ ነዉ ሲሉ ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አስታውሰዋል፡፡
በመጨረሻም መላው የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሰራተኞች የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ከመደበኛ ስራዎች ባሻገር በልዩ ትኩረት የጀነቲክ ሀብት የማንበርና ዘለቄታዊ አጠቃቀም ስራዎችን በመስራት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ምርትና ምርታማነትን የሚጨምሩ ተግባራትን ለማከናወን ቃል በመግባት የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡