You are currently viewing Discussion took place on the first quarter performance report of 2014

በ2014 ዓ.ም አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ውይይት ተደረገ

በኢትየጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የ 2014 ዓ.ም አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ከኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ጋር ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት ተደረገ፡፡

የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን አቶ ማስረሻ የማነ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ውይይቱን ዶ/ር መለሰ ማሪዮ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር የመሩት ሲሆን ከሰራተኞች ለቀረቡ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው ኃላፊዎች ምላሾች ተሰጥተው ውይይቱ መጠናቀቁን መረዳት ተችሏል፡፡