You are currently viewing Awareness creation training was given to the Ethiopian Biodiversity Institute staff

ለኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ለኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ህዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ተሰጠ፡፡

በፌደራል መንግስት መ/ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ለውጥ መሰረት የመንግስት ሰራተኞች ድልድል አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 859/2014 በአቶ እንድሪስ ሀሰን የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የቀረበ ሲሆን የሰራተኛ ድልድል አፈጻጸም፣ የትምህርት ዝግጅት፣ የውጤት ተኮር ምዘና ነጥብ አሰጣጥ፣ የፈተና ወይም ምዘና ነጥብ አፈጻጸም፣ በበላይ ኃላፊ ለአመራርነት ክህሎት የሚሰጥ ነጥብ፣ ተለዋጭ መስፈርቶች፣ ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ፣ የቅሬት አቀራረብና አፈታት ሥነ-ሥርዓት እና ሌሎች ድንጋጌዎችን ያካተተ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

የፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ዓላማዎችና መርሆዎችን ያካተተ የስልጠና ሰነድ በአቶ ብስራት ዓለማየሁ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ባለሙያ ቀርቧል፡፡ በሰነዱም የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ መርሆዎች፣ የጥቆማ መቀበያ ስርዓት፣ የህግ ማዕቀፎች፣ በተፈጥሮ ባህርያቸው ለሙስና ተጋላጭ ተጋላጭ የሚሆኑ አሰራሮች…በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

አቶ መኳንንት እያዩ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የጽ/ቤት ኃላፊ ውይይቱን የመሩ ሲሆን ከሰራተኞች ለቀረቡ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሾች ተሰጥተው ስልጠናው መጠናቀቁን መረዳት ተችሏል፡፡