You are currently viewing Ethiopia participates on CBD

ኢትዮጵያ በአለማቀፉ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት ላይ ተሳተፈች

ኢትዮጵያ አፍሪካን በመወከል ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር በካናዳ ሞንትሪያል ውይይት ተደረገ፡፡ በውይይቱም ላይ በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ በብዝሃ ህይወት ላይ ያለውን ተጽእኖን ጨምሮ የብዝሀ ህይወት መመናመን መንስኤዎች ተዳሰዋል፡፡ በቂ መጠን ያለው የሃብት ማሰባሰብ አስፈላጊነት፣ ከ2020 በኋላ ያለውን ዓለም አቀፋዊ የብዝሃ ሕይወት ማዕቀፍ በፍጥነት ማፅደቅ እና ለብዝሀ ሕይወት ስምምነት ተገቢውን ትኩረት መስጠት የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ነበሩ። ርዕሰ-ጉዳዮቹ ትኩረት ተሰጥቷቸው ተግባራዊ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡