You are currently viewing International Anti-Corruption Day was celebrated

ዓለም አቀፍ የጸረ- ሙስና ቀን በዓል ተከበረ

ዓለምአቀፍ የፀረ- ሙስና ቀን በዓል “ሙስናን መታገል በተግባር!” በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት እና በግቢ ጽዳት በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ተከበረ፡፡

አቶ ልዑልሰገድ አበበ በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የስነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሙስና ጽንሰ-ሀሳብ፣ በኢትዮጵያ የጸረ-ሙስና ትግል አስቻይ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች እንዲሁም የጸረ-ሙስና ትግል አቅጣጫዎችና የባለድርሻ አካላት ሚናን ያካተተ ሰነድ ለውይይት አቅርበዋል፡፡

ተሳታፊዎችም የተለያዩ ገንቢ ሀሳቦችን ያቀረቡ ሲሆን ሁሉም ሙስናን ለመታገል የድርሻውን ለመወጣት ዝግጁነቱን አረጋግጧል፡፡

አቶ መኳንንት እያዩ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ የውይይት መድረኩን ሲያጠቃልሉ ርዕሰ-ገዳዩን ወደ ራሳችን ወስደን ሁላችንም ሚናችንን ልንወጣ ይገባል የሚል መደምደሚያ አቅርበው የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡