በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አስተባባሪነት የተዘጋጀው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባዔ ከግንቦት 14-15 ቀን 2015 ዓ.ም በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተካሄደ፡፡
በምርምር ጉባዔው ላይ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ተመራማሪዎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ለጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢዎች፣ ድጋፍ ላደረጉ አካላትና ለጉባዔው መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ተከናውኗል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መለሰ መና የመዝጊያ ንግግር ተደርጎ ፕሮግራም መጠናቀቁ ታውቋል፡፡