በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ አስተባባሪነት ነሀሴ 05 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በዘርፉ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አስታውሰው ሰልጣኞች ለተቋማዊ ስኬት አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ እምነቴ የጎላ ነው ብለዋል፡፡
ወ/ሮ አልማዝ ከበደ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ በሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን ዘርዝረው ስልጠናውን የተመለከተ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከየማዕከላት ለመጡ ሴት ባለሙያዎች፣ ለሴት ፎረም አባላት እንዲሁም ለሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ባለሙያዎች ከኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስቴር በመጡት ከፍተኛ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ባለሙያ አቶ አብዱልጀሊል ናስር Gender Mainstreaming እንዲሁም Social Inclusion በተሰኙ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ አሳታፊ የሆነ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በቀረቡ ሰነዶች ላይ ውይይት ተደርጎ በወ/ሮ ወይኒቱ መልኩ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ማጠቃለያ ተሰጥቶ ስልጠናው መጠናቀቁ ታውቋል፡፡