You are currently viewing A closing workshop was held for the project of improving and strengthening the care of Protected Areas.

የጥብቅ ቦታዎች እንክብካቤ ማሻሻልና ማጠናከር ፕሮጀክት የመዝጊያ ወርክሾፕ ተካሄደ

የጥብቅ ቦታዎች እንክብካቤ ማሻሻልና ማጠናከር ፕሮጀክት የመዝጊያ ወርክሾፕ ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም በቢሾፍቱ ተካሄደ፡፡

ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ፕሮጀክቱ ውጤታማና ለሌሎች ፕሮጀክቶች በአርዓያነት እንደሚጠቀስ አስታውሰው ከኦዲት ግኝት ነጻ መሆኑንም በአብነት ጠቅሰዋል፡፡

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ደመቀ ዳቲኮ በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን አቅርበው የፕሮጀክቱን የቆይታ ጊዜ፣ ፕሮጀክቱ የተንቀሳቀሰባቸውን ስፍራዎች፣ የፕሮጀክቱን ዓላማና በጀት፣ በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ አካላትን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ፕሮጀክቱን የተመለከተ አጠቃላይ መረጃዎችን በተጨማሪነት አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ተሳታፊዎችም ፕሮጀክቱ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ማቀራረብ የቻለ፣ ተጨማሪ ሀብት እንዲገኝ በር የከፈተ፣ ወቅታዊ ሪፖርቶችን በየጊዜው የሚያቀርብ፣ ማዕከላትን ያሳተፈ መሆኑ፣ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ ከመደበኛ ስራዎች ጋር ተጣምሮ መሰራት እንደሚችል ገልጸው ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት ለተሳተፉ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡