የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የብሔራዊ ብዝሀ ሕይወት የመጀመሪያ የምክክር መድረክ በቢሾፍቱ ፒራሚድ ሆቴልና ሪዞርት በ02/05/2016 ዓ.ም አካሄዷል፡፡
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ምልዓተ ጉባኤዉ የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣የብሔራዊ የብዝሀ ሕይወት መድረክ አባላት፣ የፌደራልና የክልል መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የሳይንስ ቤተሰቦች፣የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አመራሮች ፣የሚዲያ ቤተሰቦች እና የመድረኩ ባለድርሻ አካላት ያካተተ እንደሆነና እንደ ብዝሀ ሕይወት መድረክ መመሪያ በዓመት ሁለት ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤዉን ያደርጋል ብለዋል፡፡ አክለዉም ይህ ጉባኤ ስለ ብዝሀ ሕይወትና ስርዓተ ምህዳር አገልግሎቶች ሪፖርቶችን በመስማት ግምገማ ያደርጋል፡፡በፖሊሲ አውጪዎች፣ ሳይንቲስቶች እና ባለሙያዎች መካከል የተሻለ መረጃን ለመለዋወጥ እቅድ ነድፎ የትብብር ተሳትፎን በማረጋገጥ በጋራ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ ስለዕለቱ መድረክ ለተሳታፊዎች እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የድህረ 2020 የብዝሀ ሕይወት ማዕቀፍ በካናዳ ሞንትሪያል ባለፈዉ ዓመት መፅደቁና ዓለምም ይህንን ለመተግበር በጥድፊያ ላይ መሆኗን ገልጸዉ እኛም እንደ ሀገር ይህንን ማዕቀፍ ተሳትፈናል፣ተቀብለናል አፅድቀናልም ብለዋል፡፡
ማዕቀፉ ከ2021 – 2030 የሚዘልቅ ሲሆን ስራዎች ይሰራሉ በየዓመቱ ሪፖርት ይደረጋሉ፡፡ የብዝሀ ሕይወትና የስርዓተ-ምህዳር ግልጋሎት በሶስት ዋና ዋና አካላት የሚፈፀም ሲሆን ፖሊሲ አዉጪዎች፣ የሳይንሱ ማህበረሰብ እና ተግባሪ አካላት መሆናቸዉን አክለዋል፡፡
“A brief review of the National Ecosystem Assessment (NEA)” በዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ እንዲሁም “Scenario Analysis based on the findings of the (NEA)” በፕሮፌሰር መኩሪያ አርጋዉ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበዋል፡፡
ዶ/ር ደመቀ ዳቲኮ “BES Net Phase Project II Overview” ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን “Assessment findings of Matters Related to “Biodiversity and Ecosystem Services (BES)” በዶ/ር አብዮት ብርሃኑ እንዲሁም “Assessment findings of Matters Related to “the National Biodiversity Platform-Ethiopia” (NBP-Ethiopia)” በዶ/ር ሳምሶን ሺመልስ ቀርቧል፡፡
“IPBES Assessment Report on Invasive Alien Species: The East African perspective” በዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር የቀረበ ሲሆን
የቡድን ውይይቶችና ሪፖርቶች ቀርበው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡



