You are currently viewing Biodiversity and Ecosystem Service Network (BES Net) project discussion forum was held

Biodiversity and Ecosystem Service Network (BES Net) ፕሮጀክት የዉይይት መድረክ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በቢሾፍቱ ፒራሚድ ሆቴል ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም BES NET ፕሮጀክት ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችል የዉይይት መድረክ አካሄደ፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማርዮ በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንደገለፁት የስርዓተ ምህዳር ዳሰሳ ጥናት ደረጃ 1 ኢትዮጵያ የላቀ አፈፃፀም በማምጣቷና የብዝሀ ሕይወት ፕላትፎርም ከ170 በላይ አባላትን ያቀፈ መሆኑን አስታውሰው ደረጃ 2 BES NET ፕሮጀክት መጀመሩን ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ በዋናነት ይህ ጥናት ትኩረት አድርጎ የሚሰራዉ ብዝሀ ሕይወትና የስነ-ምህዳር አገልግሎት ላይ መሆኑን ጠቁመዉ በዘርፉ የሚሰሩ ተቋማትን በመለየት የሚሰሩት ስራ ምን እንደሆነ ማወቅ፣ እየተሰራ ባለዉ ስራ የሚገኘዉ ግኝትና አንድምታ፣ ክፍተቶቹ እና መስተጋብራቸዉን የሚያሳይ መሆኑን ለተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡

ጥናቱን ተፈፃሚ ለማድረግ በሶስት ግብረሀይል የተዋቀረ ቡድን የሚካሄደዉን ጥናት ይዘት የሚያሳይ TOR (Terms of Reference) በቡድኑ ዋና ሰብሳቢዎች ቀርቧል፡፡

በቀረበዉ ፅሁፍ መነሻነት ከመድረኩ በተነሱ ግብዓት የሚሆኑ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ላይ ዉይይት ተካሄዷል፡፡