የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የስልጠና፣ ማማከር እና ፕሮጀክት ክትትል ድጋፍ ምርምር መሪ ስራ አስፈፃሚ ለኢንስቲትዩቱ ማዕከላት ተመራማሪዎች በቢሾፍቱ ፒራሚድ ሆቴል ከታህሳስ 22 እስከ 26/2017 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንደገለፁት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ለተቋሙ የጎላ ጠቀሜታ ያለዉ በመሆኑ በዘርፉ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ይረዳል ብለዋል፡፡
አክለዉም ተቋማዊ ተልዕኮን ለማሳካት የሚሰሩ ስራዎች ዋጋ እንዲኖራቸዉ፣ በተግባር ለመለወጥ እንዲያስችልና ቴክኖሎጂዉ በፍጥነት እየዘመነ በመምጣቱ እራስን ለማሻሻል ስራዎችን ከፍ ለማድረግ እንዲረዳ ነዉ ብለዋል፡፡
የማዕከላት እና እጽዋት አጸድ አስተባባሪ አቶ ግሩም ፋሪስ እንደተናገሩት ይህን የመሰለ ስልጠና በኢንስቲትዩቱ ሲዘጋጅ ለመጀመሪያ ግዜ በመሆኑ መልካም እድል መሆኑን ገልፀዉ ለተመራማሪዎቹ ልዩ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የስልጠና፣ማማከር እና ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ ምርምር መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሳምሶን ሽመልስ ለማዕከላት ስልጠና መስጠት ሲታሰብ በምን ዘርፍ ትኩረት ያደረገ ቢሆን ተብሎ ሲታሰብ ክፍተቶችን በመለየት በተመረጡት ላይ ስልጠናዉ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
አክለዉም በስራ ላይ በየጊዜዉ እዉቀትን በማሻሻል፣ ክፍተትን በመሙላት በተሻለ ሁኔታ የምርመር ስራዎችን ለማከናወን እንዲረዳ ነዉ ብለዋል፡፡
በኢንስቲትዩቱ ዘርፈ ብዙ ልምድ ባለቸዉ ነባር ተመራማሪዎች በResearch Methods, Project proposal and Scientific writing, Software basics (R software), Geonode oriented basic GIS tools, Setting Priorities and Engaging in research and Controlling Illegal Transfer of Genetic Resources ላይ ተግባር ተኮር የሆነ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በማዕከላት የስራ ሂደት ላይ እየታዩ ባሉ መልካም የስራ ክንዉኖችና በሚያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ከዋና የኢንስቲትዩቱ ሀላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት ጋር ሰፋ ያለ ዉይይት ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም በወሰዱት ትምህርት እና ባገኙት ልምድ መደሰታቸዉንና ለምርምር ስራዉ ልዩ እገዛ እንዳለዉ ስልጠናዉም ቀጣይነት እንዲኖረዉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩትም ለስልጣኞች የእዉቅና ሰርተፍኬት ሰጥቷል፡፡



