የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በSeeds for Resilience Project ድጋፍ በጊኒር ወረዳ ሐረዋ 1 ቀበሌ በሚገኘው የማሕበረሰብ ዘር ባንክ ውስጥ ላለፉት ሦስት ዓመታት ባካሄደው አርሶ አደርን ያሳተፈ የስንዴ ምርምር ሥራ አማካኝነት የተመረጡ አራት ነባር የስንዴ ዓይነቴዎች (farmers varieties) የመዝራት መርሀ-ግብር አከናወነ፡፡ በጊኒር ማህበረሰብ ዘር ባንክ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ከሁለት ሄክታር በሚበልጥ ማሳ ላይ አስፈላጊውን የመስክ ቅየሳ /Field layout/ በማካሄድ በምርምር የተገኙ አራት ነባር የስንዴ ዓይነቴዎች የመዝራት መርሀ-ግብር የተከናወነ ሲሆን፣ በመርሀ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች፣ የጎባ ብዝሀ ሕይወት ማዕከል ተመራማሪዎች፣ የጊኒር ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት የአዝርዕት ልማትና ጥበቃ ቡድን መሪ፣ የጊኒር ማሕበረሰብ ዘር ባንክ አባላትና የአካባቢው አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል፡፡ በምርምር ጣቢያው ለአካባቢው ሥነ-ምህዳር ተስማሚ የሆኑ፣ በሽታን መቋቋም የሚችሉ (rust disease) ፣ የምርት መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ አራት ነባር የስንዴ ዓይነቴዎች (farmers varieties) በSeeds for Resilience Project ድጋፍ በተከናወነው አሳታፊ የነባር ስንዴ ምርምር (Participatory Variety Selection) ማግኘት መቻሉ ይታወቃል፡፡
