You are currently viewing A panel discussion was held

የፓናል ውይይት ተደረገ

ዘላቂነት ለማረጋገጥ ልማትን ከብዝሀ ሕይወት ጥበቃ ጋር አስማምቶ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ። የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍን የብዝሀ ሕይወት ቀን አስመልክቶ ባዘጋጀዉ የፓናል ዉይይት ላይ ኢትዮጵያ ያላትን የብዝሀ ሕይወት ሀብት በማንበርና በዘላቂነት ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

በፓናል ዉይይቱን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ካርታ ካስኬ እንደ ሀገር የተያዘዉ እንደ አረንጓዴ አሻር ያሉ ፕሮግራሞች ለብዝሀ ሕይወት ጥበቃ ያላቸዉን አስተዋፅኦ አንስተዉ በቅርቡ በሚኒስቴሮች ምክር ቤት የፀደቀዉ የስርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ስርዓትም ተጨማሪ ጉልበት ይሆናል ብለዋል፡፡

የአየር ንብረት ለዉጥና መጤ ወራሪ ዝርያዎች ለብዝሀ ሕይወት መመናመን ምክንያት እንደሆኑ በፓናሊስቶቹ የተነሳ ሲሆን ሀብትን ከጥፋት በመታደግ ለምርትና ምርታማነት ፣ለምግብ ዋስትና ፣ለኢኮ ቱሪዝምና ለሌሎች የልማት ዘርፎች የሚያበረክታቸዉን አስተዋፅኦ ማጎበት ይገባል ተብሏል፡፡