You are currently viewing Seminar held

ሴሚናር ተካሄደ

በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የስልጠና፣ማማከር እና ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አስተባባሪነት “Life experiences and the long journeys as an example for Researcher’s staff” በሚል ርዕስ የዶ/ር ገመዶ ዳሌ የህይወት ተሞክሮና የረጅም ጊዜ ልምዶችን ያካተተ ሴሚናር ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ቀረበ፡፡

ዶ/ር ካርታ ካስኬ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ባደረጉት የመክፈቻ መልዕክት “ያለፈውን ካላወቅን የወደፊቱን የተሻለ ማድረግ ስለማይቻል ከዝነኛ ሰዎች ልምድና ስኬቶች መማር ይጠቅማል” ካሉ በኋላ መልካም የመማማሪያ መድረክ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእጽዋት ኢኮሎጂ እና ብዘሀ ህይወት ተባባሪ ፕሮፌሰር ገመዶ ዳሌ (ዶ/ር) ለስኬታቸው መሰረት የጣለው የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት መሆኑን አስታውሰው ከስኬት ብቻ ሳይሆን ከውድቀትም መማር እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም ከትውልድ ስፍራቸው እስከ ዓለምአቀፍ ደረጃ ያላቸውን ተሞክሯቸውን ዘርዝረው ተመራማሪዎች ከእሳቸው ተሞክሮ በመቅሰም ፈተናዎችን ወደ ዕድል መቀየር እንደሚያስፈልግም አስታውሰዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንት አባላትና ተመራማሪዎች ባገኙት ተሞክሮ መደሰታቸውን ገልጸው ለዶ/ር ገመዶ ዳሌ ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱም ለዶ/ር ገመዶ ዳሌ የዕውቅናና ማስታወሻ ስጦታ አበርክቶ ሴሚናሩ ተጠናቋል፡፡