በአዲስ መልክ በለማው ድረ-ገጽ ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጠ Post author:በፍቃዱ ከፈለኝ Post published:ጥቅምት 25, 2021 Post category:Uncategorized በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በአዲስ መልክ ባለማው ድረ-ገጽ ዙሪያ ለማኔጅመንት አባላት ማክሰኞ ጥቅምት 02 ቀን 2014 ዓ.ም ማብራሪያ ሰጠ፡፡ማብራሪያውን አቶ ቴዎድሮስ ወርቁ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ባቀረቡበት ወቅት ድረ-ገጹን በአዲስ መልክ ማልማት ያስፈለገበትን ምክንያት፣ ያካተታቸውን ተጨማሪ ይዘቶችና ቋንቋዎች ወዘተ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ የማኔጅመንት አባላቱም ለተከናወነው ተግባር ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ለቀረቡ የማብራሪያ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ፕሮግራሙ መጠናቀቁን መረዳት ተችሏል፡፡ ተጨማሪ ዜናዎች ብሔራዊ የፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ ተደረገ ታህሳስ 1, 2023 የተመረጡ ዘሮችን ለአርሶ አደሮች የማስረከብ መርሀ-ግብር ተከናወነ መጋቢት 12, 2025 የሰው እና የባዮስፌር ሪዘርቭ ብሔራዊ ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባ ተካሔደ ሚያዝያ 19, 2021