በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የስልጠና፣ ማማከር፣ ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አስተባባሪነት ዓርብ ነሀሴ 02 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሴሚናር ተካሄደ፡፡
ዶ/ር ሳምሶን ሺመልስ የስልጠና፣ ማማከር፣ ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ፕሮግራሙን አስተዋውቀዋል፡፡ “Fear and Beer: Linking Bird Behavior, Citizen Science, and Ecology of Hop Plantations” በሚል ርዕስ በProf. dr hab. Piotr Tryjanowski ከ Faculty of Veterinary Medicine Department of Zoology Poznan University of Life Sciences የቀረበ ሲሆን “Symphony of the River Floodplain: Understanding the diversity of waterfowl in the seasonally flooded valley of the Biebrza National Park” በሚል ርዕስ በ Prof. Dr hab. Łukasz Jankowiak ከ Institute of Biology, University of Szczecin ገለጻ ቀርቧል፡
በቀረቡት ገለጻዎች ላይ ከተመራማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበው ምላሾች ተሰጥተውባቸዋል፡፡ በሴሚናሩ ማጠቃለያ ላይ ዶ/ር ተስፉ ፈከንሳ በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የእንስሳት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ለገለጻ አቅራቢዎቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም በኢትዮጵያና በፖላንድ መካከል በትብብር የሚከናወኑ ተግባራት ሊጠናከሩ እንደሚገባ ሀሳብ አቅርበው ሴሚናሩ ተጠናቋል፡፡
