You are currently viewing Meal Sharing Program Held

የማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብር ተካሄደ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብር ነሀሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ አካሄደ፡፡

በመርሀ-ግብሩ ላይ ዶ/ር ካርታ ካስኬ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት ሰው ተኮር ተግባራት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ መሆኑን አስታውሰው እኛም በዓሉን በጋራ ማክበር ያስፈልገናል ብለዋል፡፡ አያይዘውም አዲሱ ዘመን የአብሮነት ይሁንልን በማለት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ስጦታውን ዶ/ር ካርታ ካስኬ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ለ110 ሰራተኞች አበርክተዋል፡፡