በኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ እና የልዑክ ቡድናቸው ዓርብ የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ጉብኝት አደረጉ፡፡ በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ በመገንባት ላይ ያለውን ህንጻ፣ የጂን ባንክ፣ ላቦራቶሪዎችንና ምድረ ግቢውን የጎበኙ ሲሆን በሚመለከታቸው ባለሙያዎች ገለጻና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡
ዶክተር ግርማ አመንቴ በጉብኝቱ ወቅት የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ወሳኝ የሀገሪቱን ሀብት መያዙን አስታውሰው ገጽታችንን የምንገነባበት ትልቅ ሀገራዊ አቅም ስላለው ምድረ-ግቢውን በሚጠበቀው ልክ ማልማት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይም የልማት አጋሮቻችንን በማስጎብኘት የሀገራችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ መነሻው የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት መሆኑን እናስተዋውቅበታለን ብለዋል፡፡
